ብላቴናውንም፥ “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። ብላቴናውም ተመልክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤልያስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመላለስ” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።
2 ነገሥት 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውንም ግያዝን፥ “ይህችን ሱማናዊት ጥራ” አለው። በጠራትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩን ግያዝንም፣ “ሱነማዪቱን ጥራት” አለው፤ በጠራትም ጊዜ መጥታ በፊቱ ቆመች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግያዝ ተብሎ የሚጠራውንም አገልጋዩን፥ “ሄደህ ሱነማዊትን ጥራ” አለው፤ እርሷም መጥታ በፊቱ ቆመች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግያዝ ተብሎ የሚጠራውንም አገልጋዩን፥ “ሄደህ ሱነማዊትን ጥራ” አለው፤ እርስዋም መጥታ በፊቱ ቆመች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውንም ግያዝን “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው። |
ብላቴናውንም፥ “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። ብላቴናውም ተመልክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤልያስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመላለስ” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።
ኢዮሣፍጥም፥ “በእርሱ እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የእግዚአብሔር ነቢይ በዚህ አይገኝምን?” አለ። ከእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮች አንዱ፥ “ኤልያስን እጁን ያስታጥብ የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ” ብሎ መለሰ።
እርሱም፥ “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ክብር አከበርሽኝ ምን ላድርግልሽ? ለንጉሥ ወይስ ለሠራዊት አለቃ የምነግርልሽ ጉዳይ እንዳለሽ በላት” አለው፤ እርስዋም፥ “እኔ በወገኔ መካከል እኖራለሁ” ብላ መለሰች።
ወደ ሰልሚና ሀገርም ገብተው በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማሩ፤ ዮሐንስም እየአገለገላቸው ከእነርሱ ጋር ነበር።