የእስራኤል ንጉሥም ኢዮሣፍጥን፥ “በሬማት ዘገለዓድ እንዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘምታለህን?” አለው። ኢዮሣፍጥም ለእስራእል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለው።
2 ነገሥት 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥ፥ “የሞዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞዓብ ላይ ለሰልፍ ትሄዳለህን?” ብሎ፤ ላከ። እርሱም፥ “እወጣለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አንተም እንደ እኔ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “የሞዓብ ንጉሥ ስለ ዐመፀብኝ ዐብረኸኝ ትዘምታለህን?” ሲል መልእክት ላከበት። እርሱም፣ “አዎን ዐብሬህ እዘምታለሁ፤ እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤ እንደ ሕዝብህ፤ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” በማለት መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም “የሞዓብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” የሚል መልእክት ላከ። ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “አዎ እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ አንተ፥ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፥ ፈረሶቼን እንደ ፈረሶችህ መቁጠር ትችላለህ” ሲል ከመለሰ በኋላ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም “የሞአብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” የሚል መልእክት ላከ። ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “አዎ እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ አንተ፥ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፥ ፈረሶቼን እንደ ፈረሶችህ መቊጠር ትችላለህ” ሲል ከመለሰ በኋላ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥ “የሞዓብ ንጉሥ ዐምዖብኛልና ከእኔ ጋር በሞዓብ ላይ ለሰልፍ ትሄዳለህን?” ብሎ ላከ። እርሱም “እወጣለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው፤” አለ። |
የእስራኤል ንጉሥም ኢዮሣፍጥን፥ “በሬማት ዘገለዓድ እንዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘምታለህን?” አለው። ኢዮሣፍጥም ለእስራእል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለው።
የእስራኤልም ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ፥ የኤዶምያስም ንጉሥ ሄዱ፤ የሰባትም ቀን መንገድ ዞሩ፤ ለሠራዊቱና ለሚጫኑ እንስሶች ውኃ አጡ።
የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለዓድ ትሄዳለህን?” አለው። እርሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም ለሰልፍ እንደ ሕዝብህ ናቸው፤” ብሎ መለሰለት።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።