ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ።
2 ነገሥት 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮሣፍጥም፥ “የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል” አለ። የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የኤዶምያስም ንጉሥ ወደ እርሱ ወረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮሣፍጥም፣ “የእግዚአብሔር ቃል ከርሱ ዘንድ ይገኛል” አለ፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ፣ ኢዮሣፍጥና የኤዶም ንጉሥ ዐብረው ወደ እርሱ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል” አለ፤ ከዚያም በኋላ ሦስቱም ነገሥታት ወደ ኤልሳዕ ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል” አለ፤ ከዚያም በኋላ ሦስቱም ነገሥታት ወደ ኤልሳዕ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮሣፍጥም “የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል፤” አለ። የእስራኤል ንጉሥና ኢዮሣፍጥ የኤዶምያስም ንጉሥ ወደ እርሱ ወረዱ። |
ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ።
ኢዮሣፍጥም፥ “በእርሱ እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የእግዚአብሔር ነቢይ በዚህ አይገኝምን?” አለ። ከእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮች አንዱ፥ “ኤልያስን እጁን ያስታጥብ የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ” ብሎ መለሰ።
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባትህ ነቢያትና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ፥” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ፥ “አይደለም፤ በሞዓብ እጅ ይጥላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶአልን?” አለው።
እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ ኤልሳዕ ተመለሰ፤ ወደ እርሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእስራኤል ነው እንጂ በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ ዐወቅሁ፤ አሁንም ከአገልጋይህ በረከት ተቀበል” አለው።
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈይታ ጠየቀው። ኤርምያስም፥ “አዎን አለ፤ ደግሞም በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ” አለው።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።