ሴዴቅያስም በነገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
2 ነገሥት 23:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮአክስም በነገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። እናቱም አሚጣል ትባል ነበር፥ እርስዋም የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአካዝ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። እናቱ አሚጣል ትባላለች፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአካዝም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ሦስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። እናቱም አሚጣል ትባል ነበር፤ እርስዋም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። |
ሴዴቅያስም በነገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው፥ ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣውና ስለማይመለሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦
ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።