2 ነገሥት 23:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውም የኢዮስያስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ኢዮስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዮስያስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ኀይሉም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውን እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማዪቱ እንዳመጣ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
እግዚአብሔርም፥ “እስራኤልን እንዳራቅሁት ይሁዳን ከፊቴ አርቀዋለሁ፤ ይህችንም የመረጥኋትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና፦ ስሜ በዚያ ይሆናል ያልሁትንም ቤት እጥላለሁ” አለ።
በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።