የይሁዳ ነገሥታትም በይሁዳ ከተሞች በነበሩት በኮረብታው መስገጃዎች፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ መስገጃዎች ያጥኑ ዘንድ ያኖሩአቸውን የጣዖቱን ካህናት፥ ለበዓልና ለፀሐይ፥ ለጨረቃና ለከዋክብት ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ያጥኑ የነበሩትን አቃጠላቸው።
2 ነገሥት 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ነገሥታት በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ አጠገብ በከተማው አቅራቢያ በነበረው በንጉሡ ጃንደረባ በናታን መኖሪያ አጠገብ ለፀሐይ የሰጡአቸውን ፈረሶች አቃጠለ፤ የፀሐይንም ሰረገሎች በእሳት አቃጠለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ነገሥታት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ ለፀሓይ አምልኮ የሰጧቸውን ፈረሶች ከዚያ አስወገደ። እነዚህም ናታን ሜሌክ በተባለ በአንድ ሹም ቤት አጠገብ በአደባባዩ ላይ ነበሩ። ኢዮስያስም ለፀሓይ አምልኮ የተሰጡትን ሠረገሎች አቃጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፤ ለዚሁ አምልኮ የሚያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፤ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለ ሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጽር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፤ ለዚሁ አምልኮ የሚያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፤ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጽር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም ነገሥታት በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ አጠገብ በከተማው አቅራቢያ በነበረው በጃንደረባው በናታንሜሌክ መኖሪያ አጠገብ ለፀሐይ የሰጡትን ፈረሶች አስወገደ፤ የፀሐይንም ሠረገሎች በእሳት አቃጠለ። |
የይሁዳ ነገሥታትም በይሁዳ ከተሞች በነበሩት በኮረብታው መስገጃዎች፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ መስገጃዎች ያጥኑ ዘንድ ያኖሩአቸውን የጣዖቱን ካህናት፥ ለበዓልና ለፀሐይ፥ ለጨረቃና ለከዋክብት ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ያጥኑ የነበሩትን አቃጠላቸው።
በኦሳም በምዕራብ በኩል በሸለኬት በር ሦስት፥ በምሥራቅ በኩል በዐቀበቱ በር ከጥበቃ በላይ ጥበቃ በቀን ስድስት፥ በሰሜን በኩል አራት፥ በደቡብ በኩል አራት፥ በዕቃ ቤቱ በኩል ተቀባባዮች ሁለት ሁለት፥ በምዕራብ በኩል አራት በመተላለፊያውም መንገድ ተቀባባዮች ሁለት ሁለት።
ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ የጣዖት መሠዊያዎችንና ምስሎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች።
የበዓሊምንም መሠዊያዎች በፊቱ አፈረሰ፤ በላዩም የነበሩትን ኮረብታዎችን ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የተቀረጹትንና ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች ሰባበረ፤ አደቀቃቸውም፤ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብርም ላይ በተናቸው።
ወደ ውስጠኛው አደባባይም አገባኝ፤ እነሆም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ፥ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።
ወደ ሰማይ አትመልከት፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን፥ ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ አይተህ፥ ሰግደህላቸው፥ አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።