Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ የጣ​ዖት መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ንና ምስ​ሎ​ችን አስ​ወ​ገደ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በእ​ርሱ ሥር በሰ​ላም ተቀ​መ​ጠች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከእያንዳንዱም የይሁዳ ከተሞች የማምለኪያ ኰረብቶችንና የዕጣን መሠዊያዎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በርሱ አገዛዝ ዘመን ሰላም አገኘች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችና የዕጣን መሠዊያዎቹን አስወገደ፤ መንግሥቲቱም በእርሱ ሥር ሰላም የሰፈነባት ሆነች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የኰረብታ መስገጃዎች ስፍራዎችንና ዕጣን የሚታጠንባቸውን መሠዊያዎች ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ስላስወገደ፥ በእርሱ ዘመነ መንግሥት ሰላም ሰፈነ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችና የፀሐይ ምስሎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 14:5
6 Referencias Cruzadas  

ሮብ​ዓ​ምም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ፤ በይ​ሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ሠራ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይሹ ዘንድ፥ ሕጉ​ንና ትእ​ዛ​ዙ​ንም ያደ​ርጉ ዘንድ የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ አዘዘ።


የበ​ዓ​ሊ​ም​ንም መሠ​ዊ​ያ​ዎች በፊቱ አፈ​ረሰ፤ በላ​ዩም የነ​በ​ሩ​ትን ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ችን ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች ሰባ​በረ፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፤ ይሠ​ዉ​ላ​ቸው በነ​በ​ሩት ሰዎች መቃ​ብ​ርም ላይ በተ​ና​ቸው።


መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሰ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንና የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ችም አደ​ቀቀ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የኮ​ረ​ብ​ታ​ዎ​ችን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​አ​ጠፋ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።


መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ይፈ​ር​ሳሉ፤ የፀ​ሐይ ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁም ይሰ​በ​ራሉ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎ​ቻ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እጥ​ላ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ካሳ​ረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም ዐለፈ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos