Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 31:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የሚ​ያ​በራ ፀሐይ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ጨረ​ቃም እን​ደ​ም​ት​ጨ​ልም አላ​ይ​ምን? በራ​ሳ​ቸው ለመ​ኖር ኀይል የላ​ቸ​ው​ምና፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የፀሓይን ድምቀት አይቼ፣ ወይም የጨረቃን አካሄድ ግርማ ተመልክቼ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ፀሐይ ስታበራ ጨረቃም በክብር ስትሄድ አይቼ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የፀሐይን ማሸብረቅ፥ የጨረቃን መድመቅ ተመልክቼ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ፀሐይ ሲበራ ጨረቃም በክብር ስትሄድ አይቼ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 31:26
13 Referencias Cruzadas  

የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ አጠ​ገብ በከ​ተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ በነ​በ​ረው በን​ጉሡ ጃን​ደ​ረባ በና​ታን መኖ​ሪያ አጠ​ገብ ለፀ​ሐይ የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ፈረ​ሶች አቃ​ጠለ፤ የፀ​ሐ​ይ​ንም ሰረ​ገ​ሎች በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች በነ​በ​ሩት በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ መስ​ገ​ጃ​ዎች ያጥኑ ዘንድ ያኖ​ሩ​አ​ቸ​ውን የጣ​ዖ​ቱን ካህ​ናት፥ ለበ​ዓ​ልና ለፀ​ሐይ፥ ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።


እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰ​ወ​ራል፤ አያ​በ​ራ​ምም፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም በፊቱ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ሉም።


ልቤ በስ​ውር ተታ​ልሎ እንደ ሆነ፥ በአ​ፌም ላይ እጄን አኑሬ ስሜ እንደ ሆነ፥


ይህች እንደ ማለዳ ብር​ሃን የም​ት​ጐ​በኝ፥ እንደ ጨረቃ የተ​ዋ​በች እንደ ፀሓ​ይም የጠ​ራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰ​ለፈ ሠራ​ዊት የም​ታ​ስ​ፈራ ማን ናት?


ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


ልባ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ስት፥ ፈቀቅ እን​ዳ​ትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት እን​ዳ​ታ​መ​ልኩ፥ እን​ዳ​ት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ተጠ​ን​ቀቁ።


ሄዶም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ያመ​ለከ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላላ​ዘ​ዘህ ለፀ​ሐ​ይና ለጨ​ረቃ ወይም ለሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት የሰ​ገደ ቢገኝ፥


ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos