La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት በም​ድር ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን፥ እን​ዴ​ትስ እን​ዳ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ሰም​ተ​ሃል፤ አን​ተስ ትድ​ና​ለ​ህን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ የአሦር ነገሥታት በአገሮች ሁሉ ላይ ያደረጉትን፣ ፈጽሞም እንዳጠፏቸው ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፥ እንዴትስ እንዳጠፋአቸው ሰምተሃል፤ አንተስ ትድናለህን?

Ver Capítulo



2 ነገሥት 19:11
9 Referencias Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከእጄ ያድ​ናት ዘንድ ከሀ​ገ​ሮቹ አማ​ል​ክት ሁሉ ሀገ​ሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?”


“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።


አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ ጎዛ​ንን፥ ካራ​ንን፥ ራፌ​ስን በታ​ኤ​ሴ​ቴም የነ​በ​ሩ​ት​ንም የዔ​ድ​ንን ልጆች፥ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?


ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እየ​ተ​ገ​ዳ​ደረ በእ​ር​ሱም ላይ እየ​ተ​ና​ገረ፥ “የም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እን​ዳ​ል​ቻሉ፥ እን​ዲሁ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ አም​ላክ ሕዝ​ቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይ​ች​ልም” የሚል ደብ​ዳቤ ጻፈ።