በሆሴዕም በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤልንም ወደ አሶር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር፤ በጎዛንም ወንዝ፤ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።
2 ነገሥት 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛውም ዓመት ያዛት፤ በሕዝቅያስ በስድስተኛው ዓመተ መንግሥት፥ በእስራኤል ንጉሥ በሆሴዕ በዘጠነኛው ዓመተ መንገሥት፥ ሰማርያ ተያዘች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ዓመት መጨረሻ ያዛት። ሰማርያ የተያዘችውም ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት፣ ሆሴዕ በእስራኤል ላይ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተከበበችበትም በሦስተኛው ዓመት ሰማርያ በሙሉ ተያዘች፤ ይህም የሆነው ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት፥ ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተከበበችበትም በሦስተኛው ዓመት ሰማርያ በሙሉ ተያዘች፤ ይህም የሆነው ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት፥ ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት ዓመት በኋላም ወሰዳት፤ በሕዝቅያስ በስድስተኛው ዓመት፥ በእስራኤል ንጉሥ በሆሴዕ በዘጠነኛው ዓመት፥ ሰማርያ ተያዘች። |
በሆሴዕም በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤልንም ወደ አሶር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር፤ በጎዛንም ወንዝ፤ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።
እንደ ሔማት አርፋድ፥ እንደ አርፋድ ሴፋሩሔም፥ እንደ ሴፋሩሔም ካሌና፥ እንደ ካሌናም ደማስቆ፥ እንደ ደማስቆም ሰማርያ አይደለችምን?
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአለው ዙሪያሽ ድረስ ምድርሽ ይጠፋል፥ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፤ ሀገሮችሽም ይበዘበዛሉ።”
አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።