2 ነገሥት 17:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርንም ይፈሩ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በሚኖሩበት ከተማ በሰማርያ በሠሩት በከፍታው ቦታ ጣዖቶቻቸውን አኖሩ። እግዚአብሔርንም ይፈሩ ነበር፤ ከመካከላቸውም ለኮረብታው መስገጃዎች ካህናትን አደረጉ፤ በኮረብታውም መስገጃዎች ይሠዉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን አመለኩ፤ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ወገን የመጣበትን ሕዝብ ልማድ ተከትሎ፣ በየኰረብታው ባሉት ቤተ ጣዖታት የሚያገለግሉትን ካህናት ሾመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር። ከእያንዳንዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር። ከእያንዳንዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ይፈሩ ነበር፤ ከመካከላቸውም ለኮረብታው መስገጃዎች ካህናት አደረጉ፤ በኮረብታውም መስገጃዎች ይሠዉ ነበር። |
በስምንተኛውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በልቡ ባሰበው ቀን ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች በዓል አደረገላቸው፤ ወደ መሠዊያውም ሊሠዋ ወጣ።
ከቀበሩትም በኋላ ልጆቹን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፥ “በሞትሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው በተቀበረበት መቃብር ቅበሩኝ፤ አጥንቶቼ ከአጥንቶቹ ጋር ይድኑ ዘንድ አጥንቶቼን በአጥንቶቹ አጠገብ አኑሩ፤
ከዚህም በኋላ ኢዮርብዓም ከክፋቱ አልተመለሰም፤ ነገር ግን ለኮረብታዎቹ መስገጃዎች አብልጦ ከሕዝብ ሁሉ የጣዖት ካህናትን ሾመ፤ የሚወድደውንም ሁሉ ይቀድስ ነበር፤ እርሱም ለኮረብቶቹ መስገጃዎች ካህን ይሆን ነበር።
በዚያም መቀመጥ በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሔርን አይፈሩትም ነበር፤ እግዚአብሔርም አንበሶችን ሰደደባቸው፤ ይገድሉአቸውም ነበር።
በየሕዝባቸውም አምላኮቻቸውን አደረጉ፤ ሳምራውያንም በሠሯቸው በኮረብታው መስገጃዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚኖሩባቸው ከተሞቻቸው አኖሩአቸው።
እነዚህም አሕዛብ እግዚአብሔርን ይፈሩ ነበር፤ ደግሞም የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ያመልኩ ነበር፤ ልጆቻቸውም፥ የልጅ ልጆቻቸውም አባቶቻቸው እንዳደረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲሁ ያደርጋሉ።”
በሰማርያም ከተሞች የነበሩትን፥ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ የእስራኤል ነገሥታት የሠሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ኢዮስያስ አስወገዳቸው፤ በቤቴልም እንዳደረገው ነገር ሁሉ እንዲሁ አደረገባቸው።
ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆችም ቀርበው፥ “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው።