በስምንተኛውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በልቡ ባሰበው ቀን ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች በዓል አደረገላቸው፤ ወደ መሠዊያውም ሊሠዋ ወጣ።
2 ነገሥት 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ከደማስቆ በመጣ ጊዜ መሠዊያውን አየ፤ ንጉሡም ወደ መሠዊያው ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ከደማስቆ ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ መሠዊያውን አየ፤ ቀርቦም በመሠዊያው ላይ ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ ያ መሠዊያ በትክክል መሠራቱን ለማየትና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካዝም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ ያ መሠዊያ በትክክል መሠራቱን ለማየትና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ከደማስቆ በመጣ ጊዜ መሠዊያውን አየ፤ ንጉሡም ወደ መሠዊያው ቀርቦ በእርሱ ላይ ወጣ። |
በስምንተኛውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በልቡ ባሰበው ቀን ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች በዓል አደረገላቸው፤ ወደ መሠዊያውም ሊሠዋ ወጣ።
እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮርብዓምም መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።
ካህኑም ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ እንደ ላከለት መሠዊያውን ሁሉ ሠራ፤ እንዲሁም ካህኑ ኦርያ ንጉሡ አካዝ ከደማስቆ እስኪመጣ ድረስ ሠራው።
የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉንም ቍርባን አሳረገ፤ የመጠጡንም ቍርባን አፈሰሰ፤ የደኅንነቱንም መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ላይ ረጨ።
ንጉሡም፥ “የመቱኝን የደማስቆን አማልክት እፈልጋቸዋለሁ፤ የሶርያን ንጉሥ እርሱን ረድተውታልና እኔንም ይረዱኝ ዘንድ እሠዋላቸዋለሁ” አለ። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ዕንቅፋት ሆኑ።
በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት ያጥን ዘንድ የኮረብታ መስገጃዎችን አሠራ፤ የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን አስቈጣ።