2 ነገሥት 15:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአታም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
ነገር ግን የጣዖታቱን ቤት አላስወገደም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶች ላይ ይሠዉና ያጥኑ ነበር። እርሱም የላይኛውን የእግዚአብሔርን ቤት በር ሠራ።