የቀረውም የዮአስ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ከይሁዳም ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር የተዋጋበት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
2 ነገሥት 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜስያስ ግን አልሰማም፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ባለች በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተያዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜስያስ ግን አልሰማም፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ወጣ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ምድር በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተጋጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቆጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቈጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜስያስ ግን አልሰማም፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወጣ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ባለች በቤት ሳሚስ እርስ በርሳቸው ተያዩ። |
የቀረውም የዮአስ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ከይሁዳም ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር የተዋጋበት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
የኤዶምያስንም አማልክት ስለ ፈለጉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ይሰጣቸው ዘንድ ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበረና አሜስያስ አልሰማም።
ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
አሳንና መሰማርያዋን፥ ዮጣንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ።