La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 10:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዩና የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብም ወደ በዓል ቤት ገቡ። የበ​ዓ​ል​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ “መር​ምሩ፥ ከበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ብቻ በቀር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሚ​ያ​መ​ልኩ ወገን በእ​ና​ንተ ዘንድ አንድ እንኳ እን​ዳ​ይ​ኖር ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢዩ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ጋራ ወደ በኣል ቤተ ጣዖት ገባ። የበኣልንም አገልጋዮች፣ “እንግዲህ የበኣል አገልጋዮች ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እዚህ ዐብረዋችሁ አለመኖራቸውን አረጋግጡ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህም በኋላ ኢዩ ራሱ የሬካብ ልጅ ከሆነው ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ “እንግዲህ በዚህ የሚገኙት የበዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” ሲል ተናገረ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ኢዩ ራሱ የሬካብ ልጅ ከሆነው ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ “እንግዲህ በዚህ የሚገኙት የባዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” ሲል ተናገረ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዩም የሬካብም ልጅ ኢዮናዳብ ወደ በኣል ቤት ገቡ። የበኣልንም አገልጋዮች “መርምሩ፤ ከበኣል አገልጋዮች ብቻ በቀር እግዚአብሔርን ከሚያመልኩ ወገን በእናንተ ዘንድ አንድ እንኳ እንዳይኖር ተመልከቱ፤” አላቸው።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 10:23
7 Referencias Cruzadas  

ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር።


የዕቃ ቤቱ​ንም ሹም፥ “ለበ​ዓል አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ልብ​ስን አውጣ” አለው። የሚ​ያ​ለ​ብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ልብ​ሱን አወ​ጣ​ላ​ቸው።


የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ርቡ ዘንድ ገቡ፤ ኢዩም፥ “በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ ከም​ሰ​ጣ​ችሁ ሰዎች አንድ ሰው ያመ​ለጠ እንደ ሆነ ነፍሱ በዚያ እን​ዲ​ያ​መ​ልጥ ባደ​ረ​ገው ሰው ነፍስ ፋንታ ትሆ​ና​ለች” ብሎ በውጭ ሰማ​ንያ ሰዎ​ችን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።


እነ​ርሱ ግን እን​ዲህ አሉ፥ “የወ​ይ​ኑን ጠጅ አን​ጠ​ጣም፤ አባ​ታ​ችን የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ እና​ን​ተና ልጆ​ቻ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የወ​ይን ጠጅ አት​ጠጡ ብሎ አዝ​ዞ​ና​ልና።


ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን “እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ፤” እላለሁ’ አለ።”


የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፤