2 ቆሮንቶስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳታዘጋጁ ቢያገኙአችሁ እናንተ ታፍራላችሁ ባልልም እኛ ስለ እናንተ ከነገርናቸው የተነሣ እናፍራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋራ መጥተው ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም ያን ያህል በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፥ ያን ያህል ማለታችን እንድታፍሩ ባይሆንም፥ እንዲህ በመመካታችን ግን እንድናፍር ያደርገናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ወደ እናንተ መጥተው ያልተዘጋጃችሁ ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን፤ እናንተማ በጣም ታፍራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡ፥ ያልተዘጋጃችሁም ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ፥ እናንተ እንድታፍሩ አላልንም እኛ ግን በዚህ እምነታችን እንድናፍር አይሁን። |
እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ።
ይህም ቢሆን የምናገረው ለእግዚአብሔር የሚገባ አይደለም፤ ነገር ግን ስለዚህች ትምክሕቴ እንደ ሰነፍ እናገራለሁ።
አሁንም መዋደዳችሁንና እኛም በእናንተ የምንመካበትን ሥራ በአብያተ ክርስቲያናት ፊት በግልጥ አሳዩአቸው።
እናንተ እንደምትተጉ አውቃለሁና፤ ስለዚህም “የአካይያ ሰዎች እኮ ከአምና ጀምሮ አዘጋጅተዋል” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ አመሰገንኋችሁ፤ እነሆም የእናንተ መፎካከር ብዙዎችን ሰዎች አትግቶአቸዋል።