La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከብዙ መከ​ራና ከልብ ጭን​ቀት የተ​ነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እን​ድ​ታ​ውቁ ነው እንጂ እን​ድ​ታ​ዝኑ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደዚያ ስጽፍላችሁ በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፣ በብዙም እንባ ውስጥ ነበርሁ፤ ይህንም ያደረግሁት ለእናንተ ያለኝን ጽኑ ፍቅር እንድታውቁ በማለት እንጂ እናንተን ለማሳዘን አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት፥ በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበር፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፥ በብዙ እንባም ሆኜ የጻፍኩላችሁ በጣም የምወዳችሁ መሆኔን እንድታውቁ ብዬ ነው እንጂ ላሳዝናችሁ ብዬ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 2:4
12 Referencias Cruzadas  

ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ ቅን​ዐት እቀ​ና​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ወደ እርሱ አቀ​ር​ባ​ችሁ ዘንድ ለአ​ንዱ ንጹሕ ድን​ግል ሙሽራ ለክ​ር​ስ​ቶስ አጭ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


ስለ​ዚ​ህም በሁሉ ትታ​ዘ​ዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ይህን የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋ​ችሁ ይታ​ወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደ​ለና ስለ ተበ​ደለ ሰው አይ​ደ​ለም።


ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ነ​ግ​ራ​ችሁ፥ ልዩ አካ​ሄድ የሚ​ሄዱ ብዙ​ዎች አሉና፤ አሁ​ንም እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ጠላ​ቶች እንደ ሆኑ በግ​ልጥ እያ​ለ​ቀ​ስሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።