2 ቆሮንቶስ 11:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድ አንዲት ስትቀር አምስት ጊዜ አርባ አርባ ገረፉኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድ ለአርባ ጅራፍ አንድ የቀረው ዐምስት ጊዜ ገርፈውኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድ ለአርባ ጅራፍ አንድ የቀረው አምስት ጊዜ ገርፈውኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠላሳ ዘጠኝ፥ ሠላሳ ዘጠኝ ጅራፍ አምስት ጊዜ በአይሁድ ተገርፌአለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ። |
“እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራብም ትገረፋላችሁ፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።