ሰሎሞንም ፈረሶችን ከግብፅና ከቴቁሄ ሀገር አስመጣ፤ የንጉሡም ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ከቴቁሄ ያመጡአቸው ነበር።
2 ዜና መዋዕል 9:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰሎሞንም ፈረሶች ከግብፅና ከየሀገሩ ሁሉ ይመጡለት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሎሞን ፈረሶች የመጡት ከግብጽና ከሌሎች አገሮች ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰሎሞንም ፈረሶች ከግብጽና ከየአገሩ ሁሉ ያመጡለት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ከግብጽና ከሌሎች አገሮች ሁሉ ፈረሶችን ያስመጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰሎሞንም ፈረሶችን ከግብጽና ከየአገሩ ሁሉ ያመጡለት ነበር። |
ሰሎሞንም ፈረሶችን ከግብፅና ከቴቁሄ ሀገር አስመጣ፤ የንጉሡም ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ከቴቁሄ ያመጡአቸው ነበር።
የሰሎሞን ፈረሶች መምጫ ከግብፅና ከቴቁሄ ምድር ነበር። በዋጋ ገዝተው ከቴቁሄ የሚያመጡአቸውም ከሀገር ሽማግሌዎች የሆኑ የሰሎሞን ነጋዴዎች ነበሩ።
ሄደውም ከግብፅ አንድ ሰረገላ በስድስት መቶ ብር፥ አንድንም ፈረስ በመቶ አምሳ ሰቅል ብር አመጡ፤ እንዲሁም ለኬጢያውያንና ለሦርያ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው ያመጡላቸው ነበር።
ሰሎሞንም ለሰረገሎች አራት ሺህ እንስት ፈረሶችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሰረገሎችም ከተሞች፥ ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።
ርዳታ ለመፈለግ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፥ በፈረሶችና በሰረገሎችም ለሚታመኑ ወዮላቸው! ፈረሰኞቹ ብዙዎች ናቸውና፤ በእስራኤልም ቅዱስ አልታመኑምና፤ እግዚአብሔርንም አልፈለጉምና።