Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የቀ​ረ​ውም ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው የሰ​ሎ​ሞን ነገር በነ​ቢዩ በና​ታን ታሪክ፥ በሴ​ሎ​ና​ዊ​ውም በአ​ኪያ ትን​ቢት፥ ስለ ናባ​ጥም ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢ​ዩ​ሔል ራእይ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የቀረው፣ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ሥራ፣ ጥበቡም በነቢዩ በናታን ታሪክና በሴሎናዊው በአኪያ ትንቢት እንዲሁም ባለራእዩ አዶ ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው ራእይ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ተግባራት በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ በቃላት የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሌላው የሰሎሞን ታሪክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በነቢዩ ናታን ታሪክ፥ የሴሎ ተወላጅ በሆነው በነቢዩ አኪያ ትንቢትና ስለ እስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ጭምር በሚናገረው በነቢዩ ዒዶ ራእይ ተመዝግቦ ይገኛል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:29
15 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነቢዩ ናታ​ንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እር​ሱም መጥቶ አለው፥ “በአ​ንድ ከተማ አንዱ ባለ​ጠጋ፥ አን​ዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።


ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር።


ከሳ​ሪራ ሀገር የሆነ የኤ​ፍ​ሬ​ማ​ዊው የና​ባ​ጥና ሳሩሃ የተ​ባ​ለች የመ​በ​ለት ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋይ ነበረ።


ከዚህ በኋ​ላም ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ሴሎ​ና​ዊው ነቢዩ አኪያ በመ​ን​ገድ ላይ ተገ​ና​ኘው፤ ከመ​ን​ገ​ድም ገለል አደ​ረ​ገው፤ አኪ​ያም አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር። ሁለ​ቱም በሜዳ ነበሩ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


የን​ጉ​ሡም የዳ​ዊት የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባ​ለ​ራ​እዩ በሳ​ሙ​ኤል ታሪክ፥ በነ​ቢ​ዩም በና​ታን ታሪክ፥ በባለ ራእ​ዩም በጋድ ታሪክ ተጽ​ፎ​አል።


የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከን​ጉሡ ከሰ​ሎ​ሞን ፊት ሸሽቶ በግ​ብፅ ይኖር ነበ​ርና ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከግ​ብፅ ተመ​ለሰ።


የሮ​ብ​ዓ​ምም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር እነሆ፥ በነ​ቢዩ ሰማ​ያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ሮብ​ዓ​ምም ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር።


የአ​ብ​ያም የቀ​ረው ነገ​ርና አካ​ሄዱ የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውም ቃሎች በነ​ቢዩ በአዶ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos