La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 9:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ወር​ቁ​ንና ብሩን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ፥ የዝ​ግ​ባ​ው​ንም እን​ጨት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ብዛት አደ​ረ​ገው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ በኢየሩሳሌም ብሩን እንደ ማንኛውም ድንጋይ፣ የዝግባውንም ዕንጨት ብዛት በየኰረብታው ግርጌ እንደሚበቅል ሾላ አደረገው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡም ብሩን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባውንም እንጨት ብዛት በቈላ እንደሚበቅል ሾላ አደረገው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ይቈጠር ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ብሩን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባውንም እንጨት ብዛት በቈላ እንደሚበቅል ሾላ አደረገው።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 9:27
9 Referencias Cruzadas  

በቈ​ላ​ውም ውስጥ ባሉት በወ​ይ​ራ​ውና በሾ​ላው ዛፎች ላይ ጌድ​ራ​ዊው በአ​ል​ሐ​ናን ሹም ነበረ፤ በዘ​ይ​ቱም ቤቶች ላይ ኢዮ​አስ ሹም ነበረ፤


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የሚ​ጠ​ጣ​በት ዕቃ ሁሉ የወ​ርቅ ነበረ፤ የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለ​ውም ቤቱ የሚ​ገ​ለ​ገ​ል​በት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ፤ በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ብር ከቶ አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።


“ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድን​ጋይ እን​ው​ቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እን​ቍ​ረጥ፤ ለራ​ሳ​ች​ንም ግን​ብን እን​ሥራ።”


አሞ​ጽም መልሶ አሜ​ስ​ያ​ስን አለው፥ “እኔ ላም ጠባ​ቂና በለስ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነ​ቢይ ልጅ አይ​ደ​ለ​ሁም፤


ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘን​ድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያች መን​ገድ ያልፍ ዘንድ አለ​ውና።