እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
2 ዜና መዋዕል 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ንጉሡ ግምጃ ቤቱን ጨምሮ ስለ ማንኛውም ነገር ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሰጠውን ትእዛዝ አልተላለፉም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ስለ ግምጃ ቤቶችና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች ዳዊት ለካህናትና ለሌዋውያን በሰጠው መመሪያ መሠረት አንድም ሳይቀር ሁሉም በሚገባ እንዲከናወን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም። |
እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
ከእነርሱ አንዳንዶቹ በአገልግሎቱ ዕቃዎች በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁም፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቱውም ላይ ሹሞች ነበሩ።
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
የእግዚአብሔርም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዐት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዐታቸው ያመሰግኑ ዘንድ፥ በካህናቱም ፊት ያገለግሉ ዘንድ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ በረኞቹንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።
እነሆ፥ መሠረቱ ከተጣለ ጀምሮ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት እስከ ፈጸመ ድረስ ሥራው ሁሉ የተዘጋጀ ነበረ። የእግዚአብሔርም ቤት ተፈጸመ።