2 ዜና መዋዕል 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሠዊያውንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድርጎ ነበርና በስምንተኛው ቀን የፍጻሜ በዓል አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠዊያውን ለሰባት ቀን ስለ ቀደሱና የሰባት ቀን በዓል በተጨማሪ ስላከበሩ፣ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሠዊያውን ለእግዚአብሔር የተለየ በማድረግ ሥነ ሥርዓት ላይ ሰባት ቀን አሳለፉ፤ ሌላ ሰባት ቀን በዓሉን በማክበር ከሰነበቱ በኋላ በስምንተኛው ቀን የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ። |
በዚያም ዘመን ሰሎሞን፥ ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኤማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠራው ቤት ውስጥ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ፥ ደስታም እያደረጉ ሰባት ቀን በዓሉን አከበሩ።
በሰባተኛውም ወር በሃያ ሦስተኛው ቀን ሕዝቡን ወደ ድንኳናቸው አሰናበተ፤ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለሰሎሞን፥ ለሕዝቡም ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት በልባቸው ደስ ብሎአቸው ሄዱ።
ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉንም ሰባት ቀን ያህል አደረጉ፤ በስምንተኛውም ቀን እንደ ሕጋቸው ወጡ።
ሰባት ቀን መሠዊያውን ታነጻዋለህ፤ ትቀድሰውማለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል፤ መሠዊያውንም የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።
ጾምን ቀድሱ፤ ምህላንም ዐውጁ፤ ሽማግሌዎቹንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ጩኹ።
ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ስምንተኛዋም ቀን የተቀደሰች ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቡ፤ የመሰናበቻ በዓል ነውና፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።
መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቍርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።
ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ ሰባተኛው ቀን ግን መውጫው ስለሆነ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓል ይሁን፤ ለነፍስም ከሚሠራው በቀር ሥራን ሁሉ አታድርግበት።