2 ዜና መዋዕል 6:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ በሰማይ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱም፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ምድር መልሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ሆነህ ስማ፤ የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱና ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸውም ምድር መልሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱም ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ምድር መልሳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የሕዝብህንም ኃጢአት ይቅር በማለት ለቀድሞ አባቶቻቸውና ለእነርሱ ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሰህ አግባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ በሰማይ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱም ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ምድር መልሳቸው። |
“ሕዝብህ እስራኤል አንተን ስለ በደሉ በጠላት ፊት ድል ተመትተው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት በፊትህ ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥
“አንተን ስለ በደሉ ሰማያት በተዘጉ ጊዜ፥ ዝናብም ባልዘነበ ጊዜ፥ በዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ ባዋረድሃቸውም ጊዜ ከኀጢአታቸው ቢመለሱ፥
ለአብርሃምና ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብም እሰጣት ዘንድ እጄን ወደ ዘረጋሁባት ምድር አገባችኋለሁ፤ እርስዋንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።