2 ዜና መዋዕል 33:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናሴም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አምሳ አምስት ዓመት ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናሴ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐምሳ ዐምስት ዓመት ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናሴም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ኀምሳ አምስት ዓመት ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናሴም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አምሳ አምስት ዓመት ነገሠ። |
ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትም ሁሉ በሞቱ አከበሩት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥዎቻችሁ ያስጨንቁአችኋል፤ አስጨናቂዎች ሴቶችም በላያችሁ ይሠለጥኑባችኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚያመሰግኑአችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጠፋሉ።
የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስለ አደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።