ራፋስቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?” አላቸው።
2 ዜና መዋዕል 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል እያለ ለራብ፥ ለጥምና ለሞት አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ የሚያሳስታችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቅያስ፣ ‘አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል’ ማለቱስ በራብና በጥማት እንድትሞቱ ሊያሳስታችሁ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላካችን ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል” እያለ በራብና በጥም እንድትሞቱ አሳልፎ ለመስጠት የሚያባብላችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ ‘አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦራውያን እጅ ያድነናል’ ይላችኋል፤ ነገር ግን እርሱ እንደዚህ ባለ አነጋገር እያታለለ፥ በራብና በውሃ ጥም እንድታልቁ ሊያደርጋችሁ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል” እያለ በራብና በጥም እንድትሞቱ አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ የሚያባብላችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን? |
ራፋስቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?” አላቸው።
ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል፤ ይህችንም ከተማ የአሦር ንጉሥ ሊይዛት አይችልም እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።
“ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክህ አያታልልህ።
በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ፤ በእርሱም ላይ ዕጠኑ፤ እያለ የይሁዳን ሕዝብና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች አዝዞ፥ የኮረብታውን መስገጃዎችና መሠዊያዎቹን ያፈረሰ ይህ ሕዝቅያስ አይደለምን?
አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፤ በእነዚህም ቃላት እንድትተማመኑ አያድርጋችሁ፤ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶች እጅ ያድን ዘንድ ማንም አልቻለም፤ ስለዚህም አምላካችሁ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ አይችልም።”
ራፋስቂስ ግን፥ “ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ፥ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ለተቀመጡት ሰዎች እነግራቸው ዘንድ አይደለምን?” አላቸው።
ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር ያድነናል ብሎ አያታልላችሁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት ሀገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?