ለሠራተኞችም ይከፍሉ ዘንድ ገንዘቡን የሚወስዱትን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር፤ በታማኝነት ይሠሩ ነበርና።
2 ዜና መዋዕል 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባኡንና ዐሥራቱን፥ የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡ። ሌዋዊውም ኮክንያስ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ስጦታውን፣ ዐሥራቱንና የተቀደሱ ስጦታዎቹን በታማኝነት አምጥተው አስገቡ። ሌዋዊው ኮናንያ የእነዚሁ ዕቃዎች ኀላፊ ሲሆን፣ ወንድሙ ሰሜኢ ደግሞ በማዕርግ ሁለተኛ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁርባኑና አሥራቱን የተቀደሱትንም ነገሮች በታማኝነት ወደዚያ አስገቡ። ሌዋዊውም ኮናንያ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥራቱንና በኲራቱን፥ የተቀደሱትንም ስጦታዎች ሁሉ በእምነት ወደዚያ አስገቡ፤ ኮናንያ ተብሎ የሚጠራው ሌዋዊ የዕቃ ግምጃ ቤቱ ኀላፊ ሆኖ ሲሾም፥ ወንድሙ ሺምዒ ደግሞ ረዳቱ ሆኖ ተሾመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍርባኑንና አሥራቱን የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡት። ሌዋዊውም ኮናንያ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፤ |
ለሠራተኞችም ይከፍሉ ዘንድ ገንዘቡን የሚወስዱትን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር፤ በታማኝነት ይሠሩ ነበርና።
ንጉሡም ሕዝቅያስና የእግዚአብሔር ቤት አለቃ ዓዛርያስ እንደ አዘዙ ኢዮኤል፥ ዓዛዝያ፥ አናኤት፥ ኡሳሄል፥ ኢያሪሞት፥ ኢዮዛብድ፥ ኤልሄል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስና ልጆቹ፥ ከኮክንያስና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።
ክህነት ለሚገባቸው ለአሮን ልጆች ለካህናቱ፥ በከተሞቻቸውም ዙሪያ ባሉ መሰማሪያዎችና በሌሎችም ከተሞች ላሉ ለወንዶች ሁሉ፥ ከሌዋውያን ጋራ ለተቈጠሩ ሰዎችም ሁሉ ከፍለው ይሰጡ ዘንድ በስም የተጠሩ ሰዎች ነበሩ።
የሌዋውያኑም አለቆች ኮኒንያስ በንያስም፥ ወንድሞቹም ሰማዕያስና ናትናኤል፥ ሰብንያስ፥ ኢዮሄል፥ ኢዮዛብድ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችን፥ አምስት መቶም በሬዎችን ለሌዋውያን ሰጡ።
የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ቀዳምያት፥ የመቅደሱን ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት፥ በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።