2 ዜና መዋዕል 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን እንደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አልገባም። ሕዝቡም በበደሉ እንደ ገፋበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ ጌታ መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታም አባቱ እንዳደረገው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ሠራ፤ አባቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ዕጣን በማጠን ያደረገውን ኃጢአትም አልሠራም፤ ሕዝቡ ግን ኃጢአት መሥራቱን ቀጥሎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር። |
አካዝም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አላደረገም።
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣኻቸው ሕዝብህ በድለዋልና ሂድ፤ ፈጥነህ ውረድ።
ኀጢአተኛ ወገንና ዐመፅ የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ በደለኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ተዋችሁት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጣችሁት።