La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 26:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በዓ​ለት ላይ በሚ​ኖሩ ዓረ​ባ​ው​ያን፥ በም​ዕ​ዑ​ና​ው​ያ​ንም ላይ አጸ​ናው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን፣ በጉርበኣል በሚኖሩ ዐረቦችና በምዑናውያን ላይ ድልን አቀዳጀው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍልስጥኤማውያንን፥ በጒርባዓል ይኖሩ የነበሩትን ዐረቦችና መዑናውያንን ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 26:7
14 Referencias Cruzadas  

መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


በስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ እነ​ዚ​ህም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን መጥ​ተው ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና በዚያ የተ​ገ​ኙ​ትን ምዑ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ሪያ ነበ​ርና በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።


ሰልፉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና ብዙ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ፤ እስከ ምር​ኮም ዘመን ድረስ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ አሳም ሊጋ​ጠ​መው ወጣ፤ በመ​ሪ​ሳም ደቡብ አጠ​ገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ተሰ​ለፉ።


አሳም፥ “አቤቱ፥ በብ​ዙም ሆነ በጥ​ቂቱ ማዳን አይ​ሳ​ን​ህም፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በአ​ንተ ታም​ነ​ና​ልና፥ በስ​ም​ህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥ​ተ​ና​ልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያ​ሸ​ን​ፍ​ህም” ብሎ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን ያመ​ጡ​ለት ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞ​ዓ​ብና የአ​ሞን ልጆች ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ምዑ​ና​ው​ያን ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ሊወጉ መጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን አጠ​ገብ የሚ​ኖ​ሩ​ትን የዓ​ረ​ብ​ያን ሰዎች በኢ​ዮ​ራም ላይ አስ​ነሣ።


ብት​ሄድ ግን፥ በእ​ነ​ር​ሱም ማሸ​ነ​ፍን ብታ​ስብ፥ የማ​ጽ​ና​ትና የመ​ጣል ኀይል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት ይጥ​ል​ሃል” አለው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነ​ኝና ለታ​ላ​ቁም፥ ለታ​ና​ሹም እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ እስከ ዛሬ ደረ​ስሁ፤ ይደ​ረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢ​ያት ከተ​ና​ገ​ሩት፥ ሙሴም ከተ​ና​ገ​ረው ሌላ ያስ​ተ​ማ​ር​ሁት የለም።