2 ዜና መዋዕል 26:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዖዝያንም ተቈጣ፤ በመቅደስም የሚያጥንበት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግንባሩ ላይ ለምጽ ታየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥና በእጁ ይዞ ዕጣን ለማጠን ዝግጁ የነበረው ዖዝያን ተቈጣ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው ፊት ሆኖ ካህናቱ ላይ እየተቈጣ ሳለ፣ በግንባሩ ላይ የቈዳ በሽታ ወጣበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዖዝያንም ተቈጣ፤ የሚያጥንበትም ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በጌታ ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግምባሩ ላይ ለምጽ ታየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕጣን ለማጠን ዝግጁ ሆኖ ጥናውን በእጁ እንደ ያዘ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ቆሞ የነበረው ዖዝያም በካህናቱ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ወዲያውኑ በግንባሩ ላይ የቆዳ በሽታ ታየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዖዝያንም ተቍጣ፤ የሚያጥንበትም ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቍጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግምባሩ ላይ ለምጽ ታየ። |
አሳም በነቢዩ በአናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በግዞት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አስጨነቀ።
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፥ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆም፥ በግንባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም አባረሩት፤ እርሱም ደግሞ እግዝአብሔር ቀሥፎት ነበርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ።
ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ እንደ በረዶም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፤ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።