ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል።
2 ዜና መዋዕል 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምሠራውም ቤት እጅግ ታላቅና ክቡር ይሆናልና ብዙ እንጨት ያዘጋጁልኝ ዘንድ፥ እነሆ፥ አገልጋዮች ከአገልጋዮችህ ጋር ይወጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምሠራው ቤተ መቅደስ ትልቅና እጅግ ውብ መሆን ስላለበት፣ ብዙ ጠርብ ያዘጋጁልኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ እንጨት ያዘጋጁልኛል፥ ስለ ሆነም የምሠራውም ቤት እጅግ ታላቅና ድንቅ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ እኔ ልሠራ ያቀድኩት ቤተ መቅደስ ሰፊና እጅግ የተዋበ መሆን ስለሚገባው እኔም ብዙ እንጨት ቈርጠው በማዘጋጀት የአንተን ሰዎች የሚረዱ፥ የእኔን ሰዎች ወደ አንተ ለመላክ ዝግጁ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምሠራውም ቤት እጅግ ታላቅና ድንቅ ይሆናልና ብዙ እንጨት ያዘጋጁልኝ ዘንድ፥ እነሆ፥ ባሪያዎቼ ከባሪያዎችህ ጋር ይሆናሉ። |
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል።
እነሆም፥ እንጨቱን ለሚቈርጡ ለአገልጋዮችህ ሃያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ የተበጠረ ስንዴ፥ ሃያ ሺህም የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ፥ ሃያ ሺህም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ ሃያ ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት በነጻ እሰጣለሁ።”
ደግሞም አገልጋዮችህ ከሊባኖስ እንጨት መቍረጥ እንዲያውቁ እኔ አውቃለሁና ከሊባኖስ የዝግባና የጥድ፥ የሰንደልም እንጨት ላክልኝ።
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያየ በዚያ የሚያልፍ መንገደኛ ሁሉ፦ ‘እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል።