እግዚአብሔርም፥ “ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው?” አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ።
2 ዜና መዋዕል 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስም መጣ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፥ “እኔ አታልለዋለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፥ “በምን ታታልለዋለህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አንድ መንፈስ መጥቶ፣ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም፣ ‘እኔ አሳስተዋለሁ’ አለ። “እግዚአብሔርም፣ ‘እንዴት አድርገህ?’ ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈስም መጣ፥ በጌታም ፊት ቆሞ፦ ‘እኔ አታልልዋለሁ’ አለ። ጌታም፦ ‘በምን ዓይነት መንገድ?’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻ ግን አንድ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ‘እኔ ላሳስተው እችላለሁ’ አለ፤ እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈስም መጣ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ ‘እኔ አታልልዋለሁ’ አለ። እግዚአብሔርም ‘በምን?’ አለው። |
እግዚአብሔርም፥ “ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው?” አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ።
ከዕለታት አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መላእክት በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፤ ሰይጣንም ደግሞ ከእነርሱ ጋር መጣ።
ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መላእክት መጥተው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ፥ ሰይጣን ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ከእነርሱ ጋር መጣ።
ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ከክርስቶስ የዋህነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።
ይድኑ ዘንድ የእውነት ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዐመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።