Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም መጡ፤ ሰይ​ጣ​ንም ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አንድ ቀን መላእክት በእግዚአብሔር ፊት ሊቆሙ በመጡ ጊዜ፣ ሰይጣንም መጥቶ በመካከላቸው ቆመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ የአምላክ ልጆች በጌታ ፊት ለመቆም መጡ፥ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዕለታት አንድ ቀን የሰማይ መላእክት በእግዚአብሔር ፊት በቀረቡ ጊዜ ሰይጣንም አብሮአቸው ቀረበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፥ የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፥ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 1:6
16 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።


ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።


ያን​ጊ​ዜም ሰይ​ጣን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቈ​ጥር ዘንድ ዳዊ​ትን አነ​ሣ​ሣው።


መን​ፈ​ስም መጣ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቆሞ፥ “እኔ አታ​ል​ለ​ዋ​ለሁ” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በምን ታታ​ል​ለ​ዋ​ለህ?” አለው።


ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት መጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ፥ ሰይ​ጣን ደግሞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ እን​ዲህ እን​ዳ​ታ​ስብ ተጠ​ን​ቀቅ፤ በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድ​ቅና ንጹሕ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ከክ​ፋ​ትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግ​መ​ኛም ቅን የሆነ ሰው የለ​ምና፤ አንተ ግን ሀብ​ቱን በከ​ንቱ አጠፋ ዘንድ ነገ​ር​ኸኝ።”


ከዋ​ክ​ብት በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ መላ​እ​ክቴ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ አመ​ሰ​ገ​ኑኝ


ጨለ​ማን ታመ​ጣ​ለህ ሌሊ​ትም ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም የዱር አራ​ዊት ሁሉ ይወ​ጡ​በ​ታል።


እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።


“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ።


የሄ​ኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአ​ዳም ልጅ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እና​ን​ተን ዐሥራ ሁለ​ታ​ች​ሁን መር​ጫ​ችሁ የለ​ምን? ነገር ግን ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰይ​ጣን ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos