የቀረውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራዎቹም ሁሉ፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥት ታሪክ የተጻፈ አይደለምን? ነገር ግን በሸመገለ ጊዜ እግሮቹ ታመሙ።
2 ዜና መዋዕል 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የይሁዳን ሰዎች፥ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ቅጥርም፥ ግንብም፥ መዝጊያም፥ መወርወሪያም እናድርግባቸው፤ ምድሪቱንም እንገዛታለን፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደ ፈለግነው እርሱም ይፈልገናልና፤ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል፤ ሁሉንም አከናወነልን” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ አላቸው፤ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ማማ፣ መዝጊያና መወርወሪያ ያላቸውን ቅጥሮች በዙሪያቸው እናብጅ። አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም የኛው ናት፤ እኛ ፈለግነው፤ እርሱም በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጠን” እነርሱም ሠሩ፤ ተከናወነላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳንም እንዲህ አለ፦ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፥ ቅጥርና ግንብ፥ መዝጊያና መቀርቀሪያ እናድርግባቸው፤ አምላካችንን ጌታን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም ድረስ የኛው ነች፤ እኛ ፈልገነዋል፥ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል።” እነርሱም ሠሩ ተከናወነላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳ የይሁዳን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ግንቦችን፥ ቅጽሮችንና በብረት መወርወሪያ የሚዘጉ የቅጽር በሮችን በመሥራት፥ ከተሞቻችንን እንመሽግ፤ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለ ፈጸምን፥ እነሆ፥ ምድሪቱ በቊጥጥራችን ሥር ናት፤ እግዚአብሔር ጠብቆናል፤ በሁሉም አቅጣጫ የሰላም ዋስትና ሰጥቶናል፤” ሕዝቡም ከተሞችን መሸገ፤ በለጸገም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳንም“እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ቅጥርን፥ ግንብን፥ መዝጊያን፥ መወርወሪያንም እናደርግባቸው፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ ገና በፊታችን ናት፤ እኛ ፈልገነዋል፤ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል” አለ። እነርሱም ሠሩ፤ አከናወኑም። |
የቀረውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራዎቹም ሁሉ፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥት ታሪክ የተጻፈ አይደለምን? ነገር ግን በሸመገለ ጊዜ እግሮቹ ታመሙ።
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
በይሁዳም ምሽጎች ከተሞችን ሠራ፤ እግዚአብሔርም ዕረፍት ስለ ሰጠው ምድሪቱ ጸጥ ብላ ነበር፤ በዚያም ዘመን ጦርነት አልነበረም።
በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው ዕረፍትን ሰጣቸው።
ከብንያምም ጽኑዕ ኀያል የነበረው ኤሊያዳ፥ ከእርሱም ጋር ቀስት የሚገትሩ፥ ወንጭፍ የሚወነጭፉ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤
ንጉሡ አሜስያስም የይሁዳን ሕዝብ ሰበሰበ፤ እንደ እየአባቶቻቸውም ቤቶች አቆማቸው፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ የሽህ አለቆችንና የመቶ አለቆችን አደረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰልፍም የሚወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎችን አገኘ።
ከእነርሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሠራዊት ነበሩ፤ እነዚህም ንጉሡን በጠላቱ ላይ የሚያግዙ፥ በታላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ነበሩ።
ሕዝቅያስም ሰውነቱን አጽናና፤ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊትም ከተማ የሚያወጣውን በር አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ አዘጋጀ።
ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።
እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመገለ፤ ዘመኑም ዐለፈ፤