Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 26:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ሠራ​ዊት ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ንጉ​ሡን በጠ​ላቱ ላይ የሚ​ያ​ግዙ፥ በታ​ላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በእነዚህም የሚመራ ሦስት መቶ ሰባት ሺሕ ዐምስት መቶ ሰው ያለው ሰራዊት አለ፤ ይህም ንጉሡ በጠላቶቹ ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ለመሰለፍ የሚበቃ ጠንካራ ኀይል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ንጉሡንም በጠላቱ ላይ እንዲያግዝ፥ በታላቅ ኃይል ወደ ጦርነት የሚወጣ፥ በትእዛዛቸው ሥር የነበረ ሠራዊት ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በእነርሱም ሥልጣን ሥር የንጉሡን ጠላቶች ለመመከት በቂ ችሎታ ያላቸው ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ንጉሡንም በጠላቱ ላይ ያግዝ ዘንድ፥ በታላቅ ኃይል ወደ ሰልፍ የሚወጣ፥ ከእጃቸው በታች የነበረ ሠራዊት ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 26:13
9 Referencias Cruzadas  

ሮብ​ዓ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ቤት የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞች ጐል​ማ​ሶ​ችን ሰበ​ሰበ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የሮ​ብ​ዓም መን​ግ​ሥት በጸ​ናች ጊዜ፥ እር​ሱም በበ​ረታ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ረሳ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ረሱ።


አብ​ያም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አራት መቶ ሺህ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ይዞ በእ​ርሱ ላይ ተሰ​ለፈ።


እር​ሱም የይ​ሁ​ዳን ሰዎች፥ “እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች እን​ሥራ፤ ቅጥ​ርም፥ ግን​ብም፥ መዝ​ጊ​ያም፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም እና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ገ​ዛ​ታ​ለን፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ፈለ​ግ​ነው እር​ሱም ይፈ​ል​ገ​ና​ልና፤ እር​ሱም በዙ​ሪ​ያ​ችን ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ናል፤ ሁሉ​ንም አከ​ና​ወ​ነ​ልን” አለ።


ለአ​ሳም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚ​ሸ​ከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይ​ሁዳ ሠራ​ዊት፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ፥ ቀስ​ትም የሚ​ገ​ትሩ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ የብ​ን​ያም ሰዎች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።


ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ ሰበ​ሰበ፤ እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አቆ​ማ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁሉ የሽህ አለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ችን አደ​ረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰ​ል​ፍም የሚ​ወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚ​ይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎ​ችን አገኘ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች በሰ​ልፍ ጽኑ​ዓ​ንና ኀያ​ላን የሆኑ ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ።


ዖዝ​ያ​ንም ለጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋሻና ጦር፥ ራስ ቍርና ጥሩር፥ ቀስ​ትና የሚ​ወ​ነ​ጭ​ፉ​ትን ድን​ጋይ አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos