2 ዜና መዋዕል 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብያም ኢዮርብዓምን ተከትሎ አሳደደው፤ ከእርሱም ከተሞቹን ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሳናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብያም ኢዮርብዓምን አሳድዶ የቤቴልን፣ የይሻናንና የዔፍሮንን ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ወሰደበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብያም ኢዮርብዓምን አሳደደው፥ ከእርሱም ከተሞቹን፥ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቢያ የኢዮርብዓምን ሠራዊት አሳደደ፤ ከኢዮርብዓም ከተማዎች መካከልም ቤትኤልን፥ ይሻናንና ዔፍሮንን በአካባቢያቸው የሚገኙትን መንደሮች ጭምር በድል አድራጊነት ያዘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብያም ኢዮርብዓምን አሳደደው፤ ከእርሱም ከተሞቹን ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ። |
በዚያም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ የይሁዳም ልጆች በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ነበርና አሸነፉ።
አሳም ይህን ቃልና የነቢዩን የአዳድን ልጅ የአዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ ጸና፤ ከይሁዳና ከብንያምም ሀገር ሁሉ በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከያዛቸው ከተሞች ርኵሰትን ሁሉ አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ፊት የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አደሰ።
በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሠራዊቱን አኖረ፤ በይሁዳም ሀገር፥ አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች መሳፍንቱን አስቀመጠ።
ከዚያም ወዲያ ጌታችን ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጥ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ለምድረ በዳ አቅራቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።
እናንተ ግን አትዘግዩ፤ ጠላቶቻችሁንም እስከ መጨረሻው ተከታትላችሁ ያዙአቸው፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው፤” አለ።
እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ያዙ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፤ በእነርሱም ውስጥ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉ፤ ማንንም አላስቀረም፤ በኬብሮንና በንጉሥዋም እንዳደረገው እንዲሁ በዳቤርና በንጉሥዋ አደረገ።
የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው።
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄዳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ይደርሳል፤ ወደ ኢያሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደርሳል።
በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።