2 ዜና መዋዕል 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር እነሆ፥ በነቢዩ ሰማያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ሮብዓምም ከኢዮርብዓም ጋር በዘመኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓም በዘመነ መንግሥቱ ያከናወናቸው ተግባሮች ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ነቢዩ ሸማያ በጻፈው የታሪክ መዝገብና ባለራእዩ አዶ በዘገበው የትውልድ ሐረግ ታሪክ የሚገኝ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራእዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ጦርነት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲሁም የቤተሰቡ ታሪክ በነቢዩ ሸማዕያና በነቢዩ ዒዶ ታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ ሮብዓምና ኢዮርብዓም ባለማቋረጥ ዘወትር ይዋጉ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራዕዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ሰልፍ ነበረ። |
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
ነቢዩም ሰማያ ወደ ሮብዓምና ከሱስቀም ሸሽተው በኢየሩሳሌም ወደ ተሰበሰቡት ወደ ይሁዳ መሳፍንት መጥቶ እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ ተዋችሁኝ፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ በግብፅ ንጉሥ በሱስቀም እጅ ተውኋችሁ።”
ሦስት ዓመትም በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ የእናቱም ስም መዓካ ነበረ፤ የገባዖን ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓም መካከልም ሰልፍ ነበረ።
የቀረውም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የኢዮሣፍጥ ነገሮች፥ እነሆ የእስራኤልን ነገሥታት ታሪክ በጻፈው በአናኒ ልጅ በነቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽፈዋል።
የቀሩትም ነገሮቹና ሥራው ሁሉ፥ የፊተኞቹና የኋለኞቹ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአኪያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢዩሔል ራእይ የተጻፈ አይደለምን?