አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማዪቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?
2 ዜና መዋዕል 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተፀፀተም ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ ከእርሱ ዘንድ ራቀ፤ ፈጽሞም አላጠፋውም፤ በይሁዳ መልካም ነገር ተገኝቶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓም ራሱን ዝቅ አድርጎ ስላዋረደ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ ከርሱ ተመለሰ፤ ፈጽሞም አላጠፋውም። በይሁዳም ደግሞ በጥቂቱም ቢሆን መልካም ነገር ተገኝቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱንም ባዋረደ ጊዜ የጌታ ቁጣ ፈጽሞ እንዳያጠፋው ከእርሱ ዘንድ ተመለሰ፤ በይሁዳም ደግሞ መልካም ሁኔታ ተፈጠረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሮብዓም በደሉን አምኖ ራሱን ስላዋረደ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ሙሉ በሙሉ ጒዳት አላደረሰበትም፤ እንዲያውም በይሁዳ ሁሉ ነገር መልካም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውነቱንም ባዋረደ ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ ፈጽሞ እንዳያጠፋው ከእርሱ ዘንድ ተመለሰ፤ በይሁዳም ደግሞ መልካም ነገር ተገኘ። |
አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማዪቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?
ደንገጡሮችሽም ሊቀበሉሽ ይወጣሉ፤ ልጅሽም ሞተ ይሉሻል፥ እስራኤልም ሁሉ ያለቅሱለታል፤ ይቀብሩትማል፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ በኢዮርብዓም ቤት በዚህ ልጅ መልካም ነገር ተገኝቶበታልና ከኢዮርብዓም እርሱ ብቻ ይቀበራል።
ንጉሡም ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባ ቍጥር ዘበኞች መጥተው ይሸከሙአቸው ነበር፤ መልሰውም በዘበኞች ቤት ውስጥ ያኖሩአቸው ነበር።
ነገር ግን የማምለኪያ ዐፀዶችን ከምድረ ይሁዳ አስወግደሃልና፥ እግዚአብሔርንም ትፈልግ ዘንድ ልብህን አዘጋጅተሃልና መልካም ነገር ተገኝቶብሃል” አለው።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።