እንደ እግዚአብሔር ልጆች ንጹሓንና የዋሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማያምኑና በጠማሞች ልጆች መካከል ነውር ሳይኖርባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፤
1 ጢሞቴዎስ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ ይህን ደግሞ እዘዝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም የሚነቀፍበት ነገር እንዳይኖር፣ ይህንም ትእዛዝ ለሕዝቡ ስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ እነዚህን ነገሮች ደግሞ እዘዝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ነቀፋ እንዲኖሩም እነዚህን ትምህርቶች ስጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ ይህን ደግሞ እዘዝ። |
እንደ እግዚአብሔር ልጆች ንጹሓንና የዋሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማያምኑና በጠማሞች ልጆች መካከል ነውር ሳይኖርባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፤
ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።