አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
1 ጢሞቴዎስ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው የራሱን ቤት ማስተዳደር ካላወቀበት፣ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊጠብቅ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ማንም ሰው የራሱን ቤት ማስተዳደር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የገዛ ራሱን ቤተሰብ ማስተዳደር የማይችል ከሆነ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ማስተዳደር እንዴት ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? |
አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ እንዳደረጉ ዐውቆ አልገሠጻቸውምና ስለ ልጆቹ ኀጢአት ለዘለዓለም ቤቱን እንደምበቀል አስታውቄዋለሁ።