በሮሜ ላላችሁ፥ እግዚአብሔር ለሚወዳችሁ፥ ለመረጣችሁና ላከበራችሁ ሁሉ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
1 ጢሞቴዎስ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት፣ ሰላምም ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁንልህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፦ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን። |
በሮሜ ላላችሁ፥ እግዚአብሔር ለሚወዳችሁ፥ ለመረጣችሁና ላከበራችሁ ሁሉ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤
በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።