ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
1 ሳሙኤል 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ተራራማውም ወደ ኤፍሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲልካ ምድርም አለፉ፤ አላገኙአቸውምም፤ በፋስቂም ምድር አለፉ፤ በዚያም አልነበሩም፤ በኢያሚንም ምድር አለፉ፤ አላገኙአቸውምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በኰረብታማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኙም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። እንዲሁም በብንያም ግዛት በኩል ዐለፈ፤ ሆኖም አላገኟቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኘም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። ከዚያም በብንያም ምድር በኩል አለፉ፤ ሆኖም አላገኟቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልና አገልጋዩም ተነሥተው በተራራማው የኤፍሬም አገርና በሻሊሻ ምድር በኩል አልፈው አህዮቹን መፈለግ ጀመሩ፤ ነገር ግን አህዮቹን ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አልፈው ሳያገኙአቸው ቀሩ፤ እንደገናም በብንያም ግዛት በኩል አለፉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም አህዮቹን ማግኘት አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አለፉ፥ አላገኙአቸውምም፥ በሻዕሊም ምድርም አለፉ፥ በዚያም አልነበሩም፥ በብንያም ምድርም አለፉ፥ አላገኙአቸውምም። |
ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
አንድ ሰውም ከቤትሣሪሳ ከእህሉ ቀዳምያት፥ ሃያ የገብስ እንጀራ፥ የእህልም እሸት በአቁማዳ ይዞ ወደ እግዚአብሔር ሰው መጣ፤ ኤልሳዕም አገልጋዩን፥ “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው” አለ።
ዮሐንስም በዮርዳኖስ ማዶ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን ያጠምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና፤ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ያጠምቃቸው ነበር።
የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
በዚያም ዘመን ለእስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይሁዳ ቤተ ልሔምም ዕቅብት አገባ።
በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የናሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤልዩ ልጅ ፥ የኢያርምያል ልጅ፥ ኤፍራታዊው ሕልቃና ነበረ።
የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሡና ሄዳችሁ አህዮችን ፈልጉ” አለው።