1 ሳሙኤል 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከተማዪቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነጃጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፣ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፣ “ባለራእዩ እዚህ ነውን?” ሲሉ ጠየቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዳገቱ አድርገው ወደ ከተማው ሲወጡ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው “ባለ ራእይ እዚህ አለን?” ብለው ጠየቁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቆነጃጅት ውኃውን ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፦ ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ? አሉአቸው። |
እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
እነርሱም አሉ፥ “እረኞች ሁሉ ካልተሰበሰቡና ድንጋዪቱን ከጕድጓዱ አፍ ካላነሡአት በቀር አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።”
እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ደረሰች፤ እርስዋ የአባቷን በጎች ትጠብቅ ነበርና።
ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ።
በብዙዎች ደስተኞች መካከል መሰንቆን ምቱ፤ በዚያ ለእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራን፥ በእስራኤልም ውስጥ ጽድቅንና ኀይልን ያቀርባሉ። ያንጊዜም የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማዎቹ ወረዱ።
ሳኦልም ብላቴናውን፥ “የተናገርኸው ነገር መልካም ነው፤ ና፤ እንሂድ” አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ።