1 ሳሙኤል 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻችሁንና ወይናችሁንም፥ መልካም መልካሙንም የዘይት ቦታችሁን ወስዶ ለሎሌዎቹ ይሰጣቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዕርሻችሁ፣ ከወይንና ከወይራ ተክል ቦታዎቻችሁ ምርጥ ምርጡን ወስዶ ለባለሟሎቹ ይሰጣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሻችሁ፥ ከወይንና ከወይራ ተክል ቦታዎቻችሁ ምርጥ ምርጡን ወስዶ ለባለሟሎቹ ይሰጣቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምርጥ የሆነውን የእርሻ መሬታችሁን፥ የወይን ተክል ቦታችሁንና የወይራ ተክላችሁን ሁሉ ወስዶ ለባለሟሎቹ ይሰጥባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሻችሁና ከወይናችሁም መልካም መልካሙን ወስዶ ለሎሌዎቹ ይሰጣቸዋል። |
የእስራኤልም ንጉሥ የሀገሩን አለቆች ሁሉ ጠርቶ፥ “ተመልከቱ፤ ይህም ሰው ክፉ እንዲሻ እዩ፤ ስለ ሚስቶቼ ስለ ወንዶች ልጆቼና ሴቶች ልጆቼ ላከብኝ፤ ብሬንና ወርቄን ግን አልከለከልሁትም” አላቸው።
አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይወሰድ፤ ሕዝቤ ሁሉ ከየይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆቹ ርስትን ይስጥ።”
ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ብላቴኖች፥ “ብንያማውያን ሆይ! እንግዲህ ስሙ በእውነት የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ መቶ አለቆችና ሻለቆች ያደርጋችኋልን?