1 ሳሙኤል 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየዓመቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልጌላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእነዚያም በተቀደሱ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየዓመቱ በቤቴል፣ በጌልገላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፣ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየዓመቱ በቤቴል፥ በጌልጌላና በምጽጳ እየተዘዋወረ፥ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየዓመቱም ወደ ቤትኤል፥ ጌልጌላና ምጽጳ እየሄደ በእነዚህ ስፍራዎች ይፈርድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየዓመቱም ወደ ቤቴል ወደ ጌልገላ ወደ ምጽጳም ይዞር ነበር፥ በእነዚያም ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። |
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላም አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።”
የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ምዕራብ ፋሲካን አደረጉ።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ዛሬ የግብፅን ተግዳሮት ከእናንተ ላይ አስወግጃለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
አርባም ልጆች፥ ሠላሳም የልጅ ልጆች ተወለዱለት፤ በሰባም የአህያ ግልገሎች ላይ ይቀመጡ ነበር። እስራኤልንም ስምንት ዓመት ገዛ።