በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው።
1 ሳሙኤል 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም የጩኸቱን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ጩኸት ምንድን ነው?” አለ። ሰውዬውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊም ጩኸቱን በሰማ ጊዜ፣ “የምን ጩኸት ነው?” ሲል ጠየቀ። ሰውየውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊም ጩኸቱን በሰማ ጊዜ፥ “የምን ጩኸት ነው?” ሲል ጠየቀ። ሰውየውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሊም የጩኸቱን ድምፅ ሰምቶ “ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ ያም ሰው ወሬውን ለዔሊ ለመንገር ቸኲሎ ሄደና ነገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም የጩኸቱን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ ይህ ጫጫታ ምንድር ነው? አለ። ሰውዮውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው። |
በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው።
በመጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ተናውጦ ነበርና በመንገድ ዳር በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር፤ ሰውዬውም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተማዪቱ ሁሉ ተጭዋጭዋኸች።