1 ሳሙኤል 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ተናውጦ ነበርና በመንገድ ዳር በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር፤ ሰውዬውም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተማዪቱ ሁሉ ተጭዋጭዋኸች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያ እንደ ደረሰም፣ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፣ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፣ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያ እንደደረሰም፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፥ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፥ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውዬው በደረሰ ጊዜ ልቡ ለእግዚአብሔር ታቦት ተጨንቆ የነበረው ዔሊ በመንገድ ዳር በወንበር ተቀምጦ ይመለከት ነበር። ሰውዬውም ወደ ከተማ መጥቶ ወሬውን በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ከፍተኛ ጩኸት አስተጋቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ተናውጦ ነበርና በመንገድ ዳር በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር፥ ሰውዮውም ወደ ከተማይቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተማይቱ ሁሉ ተጭዋጭዋኽች። |
በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው።
ከነዓናውያንም፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፤ ከምድርም ያጠፉናል፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?”
በሴሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነሣች። በሴሎም በእግዚአብሔር ፊት ቆመች። ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ባሰባት ጊዜ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸምግሎ፥ ደንግዞም ነበርና ጀርባው ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።