La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 30:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ደክ​መው ዳዊ​ትን ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወዳ​ል​ቻሉ፥ በቦ​ሦር ወንዝ ወዳ​ስ​ቀ​ራ​ቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሊቀ​በሉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም ወደ ሕዝቡ በቀ​ረበ ጊዜ ደኅ​ን​ነ​ቱን ጠየ​ቁት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዳዊት፣ እጅግ በመድከማቸው ምክንያት ሊከተሉት ወዳልቻሉት በቦሦር ወንዝ ቀርተው ወደ ነበሩት ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነርሱም ዳዊትንና ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እነርሱ እንደ ቀረቡም ዳዊት ሰላምታ ሰጣቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ዳዊት እጅግ በመድከማቸው ምክንያት ሊከተሉት ወዳልቻሉት በብሦር ወንዝ ቀርተው ወደነበሩት ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነርሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እነርሱ እንደ ቀረቡም ዳዊት ሰላምታ ሰጣቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊትም ደክሞአቸው በብሦር ምንጭ አጠገብ ዕረፍት በማድረግ ቈይተው ወደነበሩት ወደ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ተመልሶ ሄደ። እነርሱም ዳዊትንና ተከታዮቹን ሊቀበሉአቸው መጡ፤ ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ ደኅንነታቸውን በመጠየቅ ሰላምታ አቀረበላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ደክመው ዳዊትን ይከተሉት ዘንድ ወዳልቻሉ፥ በቦሦር ወንዝ ወዳስቀራቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፥ እነርሱም ዳዊትን ከእርሱም ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሊቀበሉ ወጡ፥ ዳዊትም ወደ ሕዝቡ በቀረበ ጊዜ ደኅንነታቸውን ጠየቀ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 30:21
7 Referencias Cruzadas  

ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር በፍ​ቅር ኑሩ።


በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤


ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ሱኮት አለ​ቆች መጥቶ፥ “ለደ​ከ​ሙት ሰዎ​ችህ እህል እን​ሰጥ ዘንድ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን? ብላ​ችሁ የተ​ላ​ገ​ዳ​ች​ሁ​ብኝ፥ ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማና እነሆ፥” አለ።


ይህ​ንም ዐሥ​ሩን አይብ ወደ ሻለ​ቃው ውሰ​ደው፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠይቅ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ።”


ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።


ዳዊ​ትም ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳ​ደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦ​ሦር ወን​ዝን መሻ​ገር ደክ​መ​ዋ​ልና በኋላ ቀሩ።


ከዳ​ዊ​ትም ጋር ከሄዱ ሰዎች ክፉ​ዎ​ቹና ዐመ​ፀ​ኞቹ ሁሉ፥ “እነ​ዚህ ከእኛ ጋር አል​መ​ጡ​ምና እየ​ራ​ሳ​ቸው ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካስ​ጣ​ል​ነው ምርኮ ምንም አን​ሰ​ጣ​ቸ​ውም” አሉ።