1 ሳሙኤል 30:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበረሃውም ውስጥ አንድ ግብፃዊ አግኝተው ወደ ዳዊት ይዘውት መጡ፤ እንጀራም ሰጡትና በላ፤ ውኃም አጠጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብጻዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት፤ የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብፃዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት። የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ግብጻዊ ወጣት ከበረሓ ሲመጣ አግኝተው ወደ ዳዊት አቀረቡት፤ እነርሱም የሚመገበው እህል ሰጥተውት በላ፤ ውሃም አጠጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበረሀውም ውስጥ አንድ ግብጻዊ አግኝተው ወደ ዳዊት ይዘውት መጡ፥ እንጀራም ሰጡትና በላ፥ ውኃም አጠጡት፥ |
ዳዊትም ከእርሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦሦር ወንዝን መሻገር ደክመዋልና በኋላ ቀሩ።
ከበለሱም ጥፍጥፍ ቍራጭ ሰጡትና በላ፤ ነፍሱም ወደ እርሱ ተመለሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም ነበርና።