ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
1 ሳሙኤል 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የዔሊ ቤት ኀጢአት በዕጣንና በመሥዋዕት ለዘለዓለም እንዳይሰረይለት ለዔሊ ቤት ምያለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቍርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቁርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የዔሊ ቤተሰብ ኃጢአት በመሥዋዕትም ሆነ በቊርባን ለዘለዓለም አይሰረይም ብዬ በመሐላ ተናግሬአለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የዔሊ ቤት ኃጢአት በመሥዋዕትና በቍርባን ለዘላለም እንዳይሰረይለት ለዔሊ ቤት ምያለሁ። |
ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ስለዚህ ሕዝብ አንተ አትጸልይ፤ ይቅር እላቸው ዘንድ አትማልደኝ፤ የእነርሱን ነገር አልሰማህምና ትለምንላቸው ዘንድ ወደ እኔ አትምጣ።”
በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፤ አነጻሁሽ፤ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።
“እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ድንኳኔን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው አንጹአቸው።
ሰውስ ሰውን ቢበድል ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩለታል፤ ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸልዩለታል?” እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወድዶአልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።